• We believe the Bible to be inspired, infallible, and authoritative word of God.

  • We believe in one God eternally existent in three persons;

    God the father, God the Son, and God the Holy Spirit.

  • We believe in the Holy Spirit who emanates from the father and the Son, who is equal in receiving worship and glory as the Father and the Son.

  • We believe in the blessed Hope, the rapture of the church at Christ’s second coming.

  • We believe that the only means of being cleansed from sin and guilt is by the shed blood, through repentance and faith in Jesus Christ.

  • We believe regeneration by the Holy spirit is essential for salvation and new life.

  • We believe in the baptism and infilling by the Holy spirit and the gifts of the Holy spirit (Act. 2;4, 1Cor. 12:9-14)

  • We believe that the Ministry of the Holy Spirit is to glorify the Lord Jesus Christ and during this age to convict men of their sins, regenerate, indwell, guide, and empower the believers for godly living and service.

  • We believe in the resurrection of the saved and the lost, the saved ones to everlasting life and the lost to everlasting damnation.

  • We believe that water Baptism and the Lord’s supper are holy ordinances to be observed by believers, but they are, however, not to be regarded as a means of salvation (1Cor. 11:23-26)

  • We believe marriage to be an institution of God between one man and one woman. (Genesis 1:27 – 28, Genesis 2:18, 21- 25)

እምነታችን

መጽሐፍ ቅዱስ

የብሉይና የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት በሙልዓት በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ታምናለች። መጽሐፍ ቅዱስ ሊታመንበት የሚገባ፡ በሰው እምነትና ሕይወት ላይ የመጨረሻ ሥልጣን ያለውና የቤተ ክርስትያን እምነትና ሥርዓት መሠረት እርሱ ብቻ መሆኑን ታምናለች።

ማቴዎስ 24፡35 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16-17 2ኛ ጴጥሮስ 1፡10-21

 እግዚአብሔር

እግዚአብሔር ዘላለማዊ፡ ፈጣሪ፡ የማይወሰን፡ ፈጹም የማይለወጥ፡ ራሱን በሦስት አካል፦

በአብ፡ በወልድ፡ በመንፈስ ቅዱስ በገለጠ በአንድ አምላክ (ሥላሴ) ታምናለች።

ዘፍጥረት 1፡26 ዘዳግም 6፡4-5 መዝሙር 138(139)፡7-12 146(147)፡5 ኢሳይያስ 40፡28

ሚልክያስ 3፡6 ዮሐንስ 17፡1 ማቴዎስ 28፡19 ዘፍጥረት 3፡22 ኢሳይያስ 6፡3-8 ሉቃስ 3፡21-22   2ኛ ቆሮንቶስ 13፡14

 እግዚአብሔር  አብ

እግዚአብሔር አብ በፍቅሩ ለሰው ልጆች ሁሉ በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደህንነት እንዳዘጋጀና እርሱን ተቀብለው ኃጢአታቸውን ለሚናዘዙ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን እንደሰጣቸው ታምናለች። ዘፍጥረት 17፡1 3፡15 ዘዳግም 6፡2-5 ኢሳይያስ 7፡14 ኢሳይያስ 53 ዮሐንስ 1፡12 ዮሐንስ 3፡16

 እግዚአብሔር ወልድ

ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አብ ዘላለማዊ ልጅ መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ ተጸንሶ ከድንግል ማሪያም መወለዱን፡ፍጽም ሰውና ፍጹም አምላክ ሆኖ መዋሀዱን፡ ኃጢአት ያልሠራ መሆኑን፡በምድር ላይ በኖረባቸው ዘመናት ድንቅ ተአምራትን ማድረጉን፡ ሰውን ለመዋጀት፡ ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ራሱን ቤዛ አድርጎ በመስቀል ላይ መሞቱን፡ መቀበሩንና በሦስተኛው ቀን ከሞት መነሳቱን፡ በከብር ማረጉን፡ ከእግዚአብሔር ሊያማልደን ዘወትር በሕይወት መኖሩን፡ የቤተ ክርስትያን መስራችና ራስ መሆኑን፡ ወደ ምድር ተመልሶ በኃይልና በክብር ለ አንድ ሺህ አመት እንደሚገዛ፡ ለፍርድም እንደሚመጣ ታምናለች። ዘፍጥረት 3፡1 ኢሳይያስ 53፡5-6 ማቴዎስ 1፡20-23 ማቴዎስ 28፡6 ሉቃስ 1፡35 ዮሐንስ 1፡1-4 ዮሐንስ 19፡34 የሐዋርያት ሥራ 17፡31 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡18-21 ኤፌሶን 5፡23 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 ዕብራውያን 1፡8 ዕብራውአያን 4፡5 ዕብራውያን 7፡25 ዕብራውያን 9፡12 1ኛ ጴጥሮስ 2፡22 ራዕይ 20፡4

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ 

መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ምልዓተ አካል እንዳለውና መለኮት መሆኑን ዓለምን ስለኃጢአት ስለጽድቅና ስለፍርድ እንደሚወቅስ በምዕመናን ውስጥ አድሮ ወደ እውነት ሁሉ እንደሚመራቸው፡ እንድሚያጽናናቸው፡ የቅድስና ኑሮ ለመኖር እንደሚያስችላቸው፡ ለአገልግሎትም ኃይልና የጸጋ ስጦታዎችን እንደሚሰጣቸው ታምናለች፡ ዛሬም ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንደሚጠመቁና በልዩ ቋንቋ(በልሳን)እንደሚናገሩ ታምናለች። ዘፍጥረት 1፡2 የሐዋርያት ሥራ 5፡35 ዮሐንስ 14፡15-17 ማርቆስ 16፡17 የሐዋርያት ሥራ 2፡3-4 የሐዋርያት ሥራ 8፡14-17 የሐዋርያት ሥራ 10፡45-46 የሐዋርያት ሥራ 19፡6-7 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡10-11 1ኛ ቆሮንቶስ 14፡4-5 ዮሐንስ 7፡37-39

የሰው አፈጣጠርና ውድቀት

እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድረን ሞላዋን ከፈጠረ በኋላ በስድስተኛው ቀን “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር”ባለው ቃል መሠረት ሰውን ከምድር አፈር እንዳበጀው የህይወትንም እስትንፋስ እፍ እንዳለበት፡ ሰውም ህያው ነፍስ ያለው ፍጥረት እንደሆነ እናምናለን።

ሰው ያለ ኃጢአት እንደተፈጠረ እናምናለን። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባለመታዘዙ በኃጢአት እንደወደቀ ከእግዚአብሔርም እንደተለየ፡ የእግዚአብሔርም ክብር እንደጎደለው የዘላለም ሞት ቅጣት ወደ ሰው ሁሉ እንደደረሰ፡ ምድርም ከሰው የተነሳ እንደተረገመች እናምናለን።

ደህንነት ወይም ዳግም መወለድ

ሰው (የወንጌል ቃል ሰምቶ)በኃጢአቱ ተጸጽቶ ንስሐ ገብቶ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በፈጸመው ሥራና በደሙ ሥርየት እንዲሁም በትንሣኤው በማመን በጸጋ ብቻ በመንፈስ ቅዱስ ዳግም መወለድ እንደሚድንና እንደሚጸድቅ፡ የእግዚአብሔር ልጅም እንደሚሆን ታምናለች። ዮሐንስ 1፡12-13

ዮሐንስ 3፡4-8 የሐዋርያት ሥራ 13፡38-39 ሮሜ 3፡20-26 ሮሜ 10፡9-10 ኤፌሶን 2፡8-9

ቅድስና (መለየት)

ምዕመናን ከዓለማዊነትና በዓለም ከሚገኝ ርኩሰት መንፈሳቸውን ነፍሳቸውንና ሥጋቸውን ለይተው ለእግዚአብሔር ክብር ኢየሱስ ክርስቶስን በመምሰል የቅድስናና የጽድቅ ኑሮ መኖር እንደሚገባቸው ታምናለች። ዮሐንስ 17፡15 ሮሜ 12፡1-2 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡14-18 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡3 ቲቶ 2፡11-14 1ኛ ጴጥሮስ 2፡9 1ኛ ዮሐንስ 2፡15-16 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡19 ገላትያ 5፡19-21 1ኛ ዮሐንስ 2፡6

የክርስቶስ ዳግም ምጽዓት

የክርስቶስ ዳግም ምጽዓት የምዕመናን ሁሉ ተስፋ መሆኑን፡ በምጽዓት ጊዜ በክርስቶስ አምነው የሞቱት እንደሚነሱ፡ በሕይወት ያሉት እንደሚለወጡና ጌታን በአየር እንደሚቀበሉት። ከዚያም በኋላ ለዘላለም በደስታ ከእርሱ ጋር እንደሚኖሩ ታምናለች። ማቴዎስ 24፡30-31 ማቴዎስ 24፡44 ማቴዎስ 25፡31 ዮሐንስ 14፡3 የሐዋርያት ሥራ 1፡11 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ራዕይ 1፡14

 መላዕክት

ቅዱሳን መላዕክት - መዝሙር 103፡4 ራዕይ 5፡11-12

  •  መንፈሳዊ ፍጥረት መሆናቸውን እናምናለን
  • የእግዚአብሔርን ሐሳብ የሚያገለግሉ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ የሚወጡና የሚገቡ፡ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ቅዱሳንንም ለማገዝ በመላክ የሚያገለግሉ ፍጥረታት ናቸው።
  • ቁጥራቸውም ወሰን የሌለው ነው።

ዲያብሎስና ርኩሳን መላዕክት

  • ዲያብሎስ (ሰይጣን) በመጀመሪያ የእግዚአብሔር መልአክ እንደነበረ በትዕቢቱ ከእግዚአብሔር ሰማያዊ መንግስት እንደተጣለ እናምናለን።
  • የእግዚአብሔር ሃሳብና የህዝቡ ጠላት እንደሆነ እናምናለን። በትዕቢቱ ከእግዚአብሔር መንግስት በተጣለ ጊዜ የተባበሩትን መላዕክት ይዞ እንደወረደ፡ እርሱና የእርሱም መላዕክት የዚህ የጨለማ ገዢዎች መሆናቸውን እናምናለን።

ፍርድ

ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻ በክብር በሚገለጥበት ጊዜ በክርስቶስ አዳኝነት ያመኑ (ጻድቃን) ከእርሱ ጋር ለዘለዓለም በመንግሥተ ሰማያት እንዲያርፉ ሲፈረድላቸው፡ በክርስቶስ አዳኝነት ያላመኑ (ኃጥአን) በዘለዓለም እሳት ውስጥ ከሰይጣንና ከጥፋት መላዕክቱ ጋር እንደሚፈረድባቸውና እንደሚጣሉ ታምናለች። ማቴዎስ 25፡31-46 ሉቃስ 13፡ 23-33 ሉቃስ 16፡ 19-30 ራዕይ 20፡10-15